"ዳታ ሸምቶ ወይም ተውሶ የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አይቻልም" – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ሰብስክራይብ

"ዳታ ሸምቶ ወይም ተውሶ የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አይቻልም" – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

''የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት'' በተሰኘው ሀገራዊ ጉባኤና ኤግዚቢሽን ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ለማንኛውም የፖሊሲ ቀረጻ ዋነኛውና መሠረታዊው ግብዓት መረጃ መሆኑን ገልጸዋል።

“ማንኛውም ፖሊሲ ዋነኛው ግብዓት ዳታ (መረጃ) ስለሆነ፤ ስላለ ብቻ ሸምተን ወይም ስላገኘን ብቻ ተውሰን ፖሊሲን ብንቀርጽ፤ ያ ፖሊሲ በተሟላ መንገድ የእኛን መሻት፣ የእኛን ፍላጎት፣ የእኛን ትልም ሊያሳካ የሚችል ነው ብሎ መውሰድ ያስቸግራል።” ብለዋል፡፡

መረጃ ወርቅን የሚተካከል ውድ የሀገር ሀብት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐቢይ፣ በውጭ አካላት መረጃ ላይ ጥገኛ መሆን የሀገርን ትልም ለማሳካት እንደሚያዳግት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

“... ስለዚህ የራስን ዳታ በተለያየ የመረጃ ምንጮች ማሰባሰብ፣ ማከማቸትና ትንተና ማድረግ መቻል ለፖሊሲ ሉዓላዊነት እንደ ትልቅ ግብዓት ይወሰዳል።"

ℹ የሀገሪቱን የመረጃ ጥራት፣ ስፋትና ተደራሽነት ለማሳደግ ሁሉም ተቋማት ቴክኖሎጂን በስፋት ሊጠቀሙ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0