ዳንጎቴ ግሩፕ በኢትዮጵያ የሚኖረውን የኢንቨስትመንት መጠን ወደ 4 ቢሊዮን ዶላር አሳደገ

ሰብስክራይብ

ዳንጎቴ ግሩፕ በኢትዮጵያ የሚኖረውን የኢንቨስትመንት መጠን ወደ 4 ቢሊዮን ዶላር አሳደገ

የዳንጎቴ ግሩፕ ፕሬዝዳንት አሊኮ ዳንጎቴ የጎዴ የማዳበሪያ ፋብሪካን በጎበኙበት ወቅት፣ የአኅጉሪቱን የምግብ ሉዓላዊነት በተግባር ለማረጋገጥ ኩባንያቸው በኢትዮጵያ የሚያደርገውን ኢንቨስትመንት ከ2.5 ቢሊዮን ዶላር ወደ 4 ቢሊዮን ዶላር ማሳደጉን አስታውቀዋል፡፡

የኢንቨስትመንቱ መስፋፋት ፦

የ110 ኪሎ ሜትር የጋዝ መስመር ዝርጋታ፣

የ120 ሜጋ ዋት የኃይል ማመንጫ፣

የፓኬጂንግ (የማሸጊያ ቀረጢት) ፋብሪካ እና የ2 ሚሊዮን ቶን የኤንፒኬ ማዳበሪያ ማቀላቀያ ማዕከልን ጨምሮ በርካታ ሰፋፊ መሠረተ ልማቶችን ያካትታል፡፡

ዳንጎቴ በንግግራቸው፣ አፍሪካ ሰፊ የግብርና አቅም እያላት አሁንም ድረስ በምግብ እጥረት የምትፈተነው አርሶ አደሩ በቂ የማዳበሪያ አቅርቦት ስለማያገኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

“አፍሪካ ማዳበሪያ ላይ ትኩረት አድርጋ ከሠራች ራሷን መመገብ ብቻ ሳይሆን ለተቀረው ዓለም ከፍተኛ የግብርና ምርት መላክ የምትችልበት ትልቅ አቅም እንዳላትና በኢትዮጵያ የሚገነባው የ3 ሚሊዮን ቶን ዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካም ይህንን አኅጉራዊ ራዕይ ለማሳካትና የሕዝቦችን ብልጽግና ለማረጋገጥ የተወጠነ ስትራቴጂካዊ ምሰሶ” ነው ሲሉም አስገንዝበዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0