በኬንያ በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ሳቢያ አገር አቀፍ የተሽከርካሪዎች አድማ እና የትራንስፖርት መቋረጥ ተከሰተ - የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ

ሰብስክራይብ

በኬንያ በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ሳቢያ አገር አቀፍ የተሽከርካሪዎች አድማ እና የትራንስፖርት መቋረጥ ተከሰተ - የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ

የኢነርጂ እና ፔትሮሊየም ቁጥጥር ባለሥልጣን ግንቦት 6 ቀን የናፍጣ ዋጋን በአንድ ሊትር በ46.29 የኬንያ ሺሊንግ (ወደ 0.36 ዶላር ገደማ) ለመጨመር ባስተላለፈው ውሳኔ ተከትሎ፣ የሚኒባስ ባለቤቶች ማኅበርን፣ የቱሪስት ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎችን እና የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችን ጨምሮ በትራንስፖርት ዘርፍ ጥምረት ሥር ያሉ 14 ቡድኖች ይህንን የሥራ ማቆም አድማ ጠርተዋል።

በጥምረቱ የቀረቡት ጥያቄዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

🟠 የኢነርጂ እና ፔትሮሊየም ቁጥጥር ባለሥልጣን በግንቦት 6 ያደረገው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እንዲሰረዝ፤ የቤንዚን እና ናፍጣ ዋጋ በአንድ ሊትር ወደ 152 የኬንያ ሺሊንግ (ወደ 1.17 ዶላር ገደማ) እንዲቀንስ፣

🟠 በመንግሥታት መካከል የሚደረገው የነዳጅ ግዥ ሥርዓት እንዲቀር እና ተወዳዳሪ የገበያ ሥርዓት እንዲመለስ፣

🟠 የኢነርጂ እና ፔትሮሊየም ካቢኔ ጸሐፊ (ሚኒስትር) ኦፒዮ ዋንዳዪ ከሥራቸው እንዲለቁ፤ ባለሥልጣኑ እንዲፈርስና ገለልተኛ ተቆጣጣሪ ተቋም እንዲቋቋም፣

🟠 የሚኒባስ ተሽከርካሪዎች እንዲቃጠሉ ምክንያት የሚሆኑ የገንዘብ ዝርፊያዎችን እና “የመንጋ ፍርድ” እርምጃዎችን ለማስቆም ደህንነት እንዲጠናከር።

በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ዋና ዋና አካባቢዎች፦

1⃣ ቲካ ሱፐርሃይዌይ፦ ተቃዋሚዎች ሮይሳምቡ እና ኪሁ ንጉሮ/ሩይሩ ባይፓስን ጨምሮ የተወሰኑ የመንገድ ክፍሎችን ዘግተዋል፡፡

2⃣ ናይሮቢ፦ አሽከርካሪዎች ሞይ አቬኑ እና ቶም ምቦያ ጎዳናዎችን ከአገልግሎት አግደዋል፡፡

3⃣ የናይሮቢ የከተማ ዳርቻዎች፦ በኪቴንጌላ፣ ኦንጋታ ሮንጋይ እና ኪኑ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ቆሟል፡፡

4⃣ ምስራቃዊ ክፍሎች፦ በካሪዮባንጊ፣ አውተር ሪንግ ሮድ እና በምዊኪ መስመር ላይ ከፍተኛ የትራፊክ መዘጋት አጋጥሟል፡፡

5⃣ ሌሎች ማዕከላት፦ ናኩሩን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች የመንገድ መዘጋቶች እና የትራንስፖርት እጥረቶች መከሰታቸው ተዘግቧል።

የኬንያ ብሔራዊ ፖሊስ አገልግሎት በአገር አቀፍ ደረጃ የፀጥታ ኃይሎችን ስምሪት ያሳደገ ሲሆን፣ ሁከት በሚፈጥሩ ድርጊቶች እና ሕገ-ወጥ የመንገድ መዝጋት እንቅስቃሴዎች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0