የአዋሽ - ኮምቦልቻ - ሃራ ገበያ የባቡር መስመር ፕሮጀክት ግንባታ ከ5 ዓመታት በኋላ ዳግም ወደ ሥራ መግባቱ ተዘገበ
15:53 18.05.2026 (የተሻሻለ: 15:54 18.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአዋሽ - ኮምቦልቻ - ሃራ ገበያ የባቡር መስመር ፕሮጀክት ግንባታ ከ5 ዓመታት በኋላ ዳግም ወደ ሥራ መግባቱ ተዘገበ
የሀገሪቱን ማዕከላዊ እና ምስራቃዊ ክፍል ከሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ጋር የሚያስተሳስረው ፕሮጀክቱ በ2007 ዓ.ም ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም የፀጥታ ችግር ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ተስተጓጉሎ መቆየቱን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
392 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የባቡር መንገድ በፕሮጀክቱ ዳግም ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች ተገኘተዋል፡፡
ከወራት በፊት የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የአዋሽ - ኮምቦልቻ - ሃራ ገበያ እና የሃራ ገበያ - መቀሌ የባቡር መስመሮች ግንባታ ዳግም ሊያስጀምር እንደሆነ መግለጹ ይታወሳል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X