የሩሲያ እና የኢኳቶሪያል ጊኒ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሞስኮ የሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ - ዋና ዋና ነጥቦች፦

© telegram sputnik_ethiopiaየሩሲያ እና የኢኳቶሪያል ጊኒ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሞስኮ የሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ - ዋና ዋና ነጥቦች፦
የሩሲያ እና የኢኳቶሪያል ጊኒ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሞስኮ የሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ - ዋና ዋና ነጥቦች፦ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.05.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያ እና የኢኳቶሪያል ጊኒ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሞስኮ የሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ - ዋና ዋና ነጥቦች፦

የምዕራባውያን ማዕቀቦች በሌሎች ኪሳራ ለመኖር የሚያስችሉ መሣሪያዎች ናቸው ሲሉ ሚኒስትር ላቭሮቭ ለስፑትኒክ አፍሪካ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ገልጸዋል፡፡

ኢኳቶሪያል ጊኒ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አፍሪካን የራሷን ጉዳይ በራሷ ማስተዳደር የምትችል ነፃ አኅጉር አድርጎ እንዲቀበላት ጥሪ ታቀርባለች ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦዮኖ ለስፑትኒክ አፍሪካ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ተናግረዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦዮኖ ሩሲያ በአፍሪካ በተለይም በሳኅል ቀጣና ሰላም እንዲሰፍን ለምታደርገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በአፍሪካ ኅብረት አባል አገራት ዘንድ አብዛኞቹ በ3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ እንደሚወከሉና አንዳንዶቹም በከፍተኛ የመሪዎች ደረጃ እንደሚገኙ ላቭሮቭ እርግጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ሩሲያ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ በነዳጅ እና ጋዝ ዘርፎች ላይ የጋራ ትብብር ለማድረግ ሰፊ ዕድሎች እንዳሉ ያያሉ ሲሉ ላቭሮቭ ተናግረዋል፡፡

ሽብርተኝነት በአፍሪካ እየተስፋፋ ይገኛል፤ የዓለም ማኅበረሰብ አኅጉሪቱ ይህንን መቅሰፍት እንድትዋጋ መርዳት አለበት ሲሉ ላቭሮቭ ገልጸዋል፡፡

ላቭሮቭ በኢኳቶሪያል ጊኒ አቻቸው የቀረበላቸውን የአገሪቱን የጉብኝት ግብዣ ተቀብለዋል፡፡

ሩሲያ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ በኑክሌር ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚያደርጉትን ሥራ ለማጠናከር ተስማምተዋል ሲሉ ላቭሮቭ አስታውቀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0