ታንዛኒያ 3 ሚሊዮን ሕዝብን ለማገናኘት የሚያስችለውን የ11.2 ሚሊዮን ዶላር የገጠር ቴሌኮም ፕሮጀክት ይፋ አደረገች

ታንዛኒያ 3 ሚሊዮን ሕዝብን ለማገናኘት የሚያስችለውን የ11.2 ሚሊዮን ዶላር የገጠር ቴሌኮም ፕሮጀክት ይፋ አደረገች
የመንግሥት የገጠር ኮሙኒኬሽን ማስፋፊያ መርሐ-ግብር በደረጃ 10 ፣ በቂ የግንኙነት አገልግሎት በማያገኙ አካባቢዎች 287 የኮሙዩኒኬሽን ማማዎችን እየገነባ መሆኑን የዓለም አቀፍ ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተደራሽነት ፈንድ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አልበርት ሪቻርድ አስታውቀዋል።
እ.ኤ.አ በታኅሣሥ ወር 2025 የተጀመረውና ለ15 ወራት የሚቆየው ይህ ፕሮጀክት፤ ምዋንዛ ፣ ሩክዋ ፣ ማንያራ እና ዛንዚባርን ጨምሮ በታንዛኒያ ክልሎች የሚገኙ 287 ወረዳዎችን ተደራሽ የሚያደርግ ሲሆን፣ በ359 መንደሮች የሚኖሩ ወደ 3 ሚሊዮን ገደማ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።
ኤርቴል፣ ቮዳኮም፣ ያዝ እና ቲቲሲ የተሰኙት የቴሌኮም ኩባንያዎች የማማዎቹን ግንባታ ወደ ሥራ የሚቀይሩት ይሆናል። ይህ ተነሳሽነት 8.5 ሚሊዮን ታንዛኒያውያንን ያገናኘውን እና በቅርቡ የተጠናቀቀውን የ758 ማማዎች ፕሮጀክትን ተከትሎ የመጣ ነው።
ተቋሙ በአሁኑ ወቅት የኮሙኒኬሽን ማማዎቹን ወደ 3ጂ/4ጂ ደረጃ እያሳደገ ከመሆኑም በላይ በትምህርት ቤቶች ያለውን የዲጂታል ተደራሽነት እያስፋፋ እንደሚገኝና ይህም ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች የሚሆኑ የመርጃ መሣሪያዎችን ማካተቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ጠቅሰዋል።
የደረጃ 11 ፕሮጀክት በሌሎች ቁልፍ የመሠረተ-ልማት አውታሮች ላይ ተግባራዊ እንዲሆን መታቀዱን ሪቻርድ በማጠቃለያቸው ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X