የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠርጣሪ በ93 ዓመታቸው በቁጥጥር ስር እንዳሉ ማረፋቸውን የተባበሩት መንግሥታት ፍርድ ቤት አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopiaየቀድሞው የሩዋንዳ ነጋዴ ፌሊሲየን ካቡጋ እ
የቀድሞው የሩዋንዳ ነጋዴ ፌሊሲየን ካቡጋ እ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.05.2026
ሰብስክራይብ
የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠርጣሪ በ93 ዓመታቸው በቁጥጥር ስር እንዳሉ ማረፋቸውን የተባበሩት መንግሥታት ፍርድ ቤት አስታወቀ

የቀድሞው የሩዋንዳ ነጋዴ ፌሊሲየን ካቡጋ እ.ኤ.አ በ1994 በሩዋንዳ በቱትሲዎች ላይ በተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ወቅት የዘር ማጥፋት፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈጸም ማሴር፣ ለዘር ማጥፋት መቀስቀስ እና በሰብዓዊነት ላይ ለተፈጸሙ ወንጀሎች ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር የተባበሩት መንግሥታት (ተመድ) ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የክስ ሂደቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

ለሩዋንዳ የተቋቋመው ዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ችሎት እ.ኤ.አፐበ2013 የእስር ማዘዣ አውጥቶባቸዋል፡፡

ካቡጋ እ.ኤ.አ. በግንቦት ወር 2020 በፈረንሳይ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

እ.ኤ.አ. በጥቅምት ወር 2020 በሔግ ወደሚገኘው ዓለም አቀፍ የፍርድ ቤቶች የክርክር መድረክ ተዛውረዋል፡፡

የፍርድ ሂደቱ እ.ኤ.አ. በመስከረም ወር 2022 ተጀምሮ ነበር።

በኋላ ላይ ግን፣ የተመድ ፍርድ ቤት ለፍርድ ለመቅረብ የሚያስችል የጤና ብቃት እንደሌላቸው ማወጁን መግለጫው ጠቅሷል።

ተለቅቀው በጊዜያዊነት እንዲቆዩ ለመቀበል ፈቃደኛ የሆነ አገር ባለመኖሩ ምክንያት፣ ተጠርጣሪው በሔግ በተመድ ቁጥጥር ስር ቆይተው እንደነበር የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች አመላክተዋል። ካቡጋ ቅዳሜ ዕለት በኔዘርላንድስ በሕክምና ላይ ሳሉ ሕይወታቸው አልፏል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0