የሀገር ውስጥ የክፍያ ሥርዓቶች የአፍሪካን የአሜሪካን ዶላር ጥገኝነት በ40 በመቶ ሊቀንሱ ይችላሉ – የልማታዊ ፋይናንስ ባለሙያ

ሰብስክራይብ

የሀገር ውስጥ የክፍያ ሥርዓቶች የአፍሪካን የአሜሪካን ዶላር ጥገኝነት በ40 በመቶ ሊቀንሱ ይችላሉ – የልማታዊ ፋይናንስ ባለሙያ

አፍሪካ የራሷን ሕጎች ማውጣት እንዳለባት የልማት ፋይናንስ ባለሙያ እና የዚምባብዌ ሴቶች ማይክሮፋይናንስ ባንክ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ማንዳስ ማሪካንዳ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

“ቀደም ሲል እንዳደረግነው ሁሉ የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና አንዱ ማሳያ ነው። ነገር ግን ከአፍሪካ አኅጉራዊ የንግድ ቀጣና ጋር አብሮ የሚሄድ የአፍሪካ የክፍያ እና የመክፈያ (የገንዘብ ልውውጥ) ሥርዓት መኖሩን ማረጋገጥ አለብን።”

የአፍሪካ የብድር ደረጃ መመዘኛ ኤጀንሲ በማጠናከር በኤስ ኤንድ ፒ (S&P) እና በሙዲስ (Moody) ከፍተኛ ዋጋ አሰጣጥ ላይ ያለው ጥገኝነት ማቆም ይቻላል ብለዋል፡፡ 

የአፍሪካ የባንክ ዘርፍ የገቢ መጠን ከ100 ቢሊዮን ዶላር በላይ ማለፉን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት እንደተናገሩት፣ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ የየፋይናንስ ቴክኖሎጂ (ፊንቴክ) አጋርነቶች እና የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽነትን ማስፋፋት በአኅጉሪቱ ላይ የበለጠ ንቁ፣ ተንቀሳቃሽ እና ሁሉንም ያካተተ የባንክ ሥነ-ምኅዳር እንዲፈጠር እያደረጉት ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0