ኢትዮጵያ በ20 ኪሎ ሜትር እርምጃ ውድድር በሁለቱም ፆታ ባለድል ሆነች
20:04 16.05.2026 (የተሻሻለ: 20:14 16.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በ20 ኪሎ ሜትር እርምጃ ውድድር በሁለቱም ፆታ ባለድል ሆነች
በጋና አክራ እየተካሄደ በሚገኘው 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ20 ኪሎ ሜትር የእርምጃ ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ወርቅ በመውሰድ ደምቃ ውላለች፡፡
በወንዶች፦
ምስጋናው ዋቁማ - አንደኛ በመውጣት የአፍሪካ ሻምፒዮና ክብሩን ለተከታታይ ሁለተኛ ጊዜ አስጠብቋል፡፡
አብዱልሰላም አብዱልዋሂብ - 3ኛ ደረጃን በመያዝ ለኢትዮጵያ የነሃስ ሜዳሊያ አምጥቷል።
በሴቶች፦
ውብዓለም ሽጉጤ - ድንቅ ብቃቷን በማሳየት ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቃ ወርቅ አጥልቃለች!
የዛሬን ድሎች ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ቁጥር 5 መድረሱን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia