አሜሪካ ደቡብ አፍሪካን ከቡድን 20 ሁነቶች አግልላለች - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

አሜሪካ ደቡብ አፍሪካን ከቡድን 20 ሁነቶች አግልላለች - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላሞላ ይህን የዋሽንግተን ድርብ መስፈርት በዴሊሂ እየተካሄደ ካለው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ አጋልጠዋል።

አሜሪካ ደቡብ አፍሪካን ከቡድን 20 ክንውኖች ለማግለል የወሰደችው እርምጃ አሳሳቢ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው፤ አሁንም ቢሆን አፍሪካ እና ደቡባዊ ዓለም እንደ እኩል አጋር እንደማይታዩ ያሳያል ሲሉ ሮናልድ ላሞላ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ደቡብ አፍሪካ ሙሉ የቡድን 20 አባል መሆኗን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ በመድረኩ መስራች ሕጎች መሠረት ሊቀመንበሩም ቢሆን የትኛውም አገር በብቸኝነት የሌላኛውን አባል ተሳትፎ በአንድ ወገን ሊያግድ እንደማይችል አፅንዖት ሰጥተዋል።

ፕሪቶሪያ አሜሪካን ጨምሮ ሁሉንም አገራት በቡድን 20 ስብሰባዎቿ ላይ በደስታ ስትቀበል የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን የደቡብ አፍሪካ ልዑካን በአሜሪካ መሬት ላይ በሚደረጉ ሁነቶች ለመሳተፍ እንቅፋቶች እየገጠሟቸው መሆኑን ከፍተኛ ዲፕሎማቱ ጠቅሰዋል።

ይሁን እንጂ ደቡብ አፍሪካ ለቡድን 20 የሥራ ሂደት ያላትን ቁርጠኝነት እንደቀጠለችበትና ሌሎች አባላት ለዚህ ማግለል እርምጃ ምን ዓይነት ምላሽ እንደሚሰጡ ለመስማት እንደምትጠባበቅ ላሞላ አክለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0