የአሜሪካ እና የናይጄሪያ ጦር ኃይሎች በአፍሪካ የአይ ኤስ* ሁለተኛ አዛዥ የነበረውን ግለሰብ መደምሰሳቸውን ትራምፕ አስታወቁ

© telegram sputnik_ethiopiaየአሜሪካ እና የናይጄሪያ ጦር ኃይሎች በአፍሪካ የአይ ኤስ* ሁለተኛ አዛዥ የነበረውን ግለሰብ መደምሰሳቸውን ትራምፕ አስታወቁ
የአሜሪካ እና የናይጄሪያ ጦር ኃይሎች በአፍሪካ የአይ ኤስ* ሁለተኛ አዛዥ የነበረውን ግለሰብ መደምሰሳቸውን ትራምፕ አስታወቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.05.2026
ሰብስክራይብ

የአሜሪካ እና የናይጄሪያ ጦር ኃይሎች በአፍሪካ የአይ ኤስ* ሁለተኛ አዛዥ የነበረውን ግለሰብ መደምሰሳቸውን ትራምፕ አስታወቁ

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ “በላቀ ብቃት የተከናወነውን” የጋራ ወታደራዊ ዘመቻ ያደነቁ ሲሆን፣ የተደመሰሰውን ግለሰብም “በዓለም ላይ እጅግ ንቁ የነበረ አሸባሪ” ሲሉ ጠርተውታል።

አቡ ቢላል አል-ሚኑኪ የተባለው ይህ የናይጄሪያ ዜግነት ያለው ግለሰብ፣ በአፍሪካ አኅጉር ውስጥ ተሸሽጎ የነበረ ሲሆን ከ2023 ጀምሮ በአሜሪካ ማዕቀብ ተጥሎበት የቆየ ነበር።

ትራምፕ ናይጄሪያ ላደረገችው አጋርነት ምስጋናቸውን ያቀረቡ ቢሆንም፣ ስለ ጥቃቱ ቦታም ሆነ ስለተፈጸመበት መንገድ የተሰጠ ዝርዝር መረጃ የለም።

*በሩሲያ እና በብዙ የዓለም አገራት የታገደ የአሸባሪዎች ድርጅት

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0