ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ተቋማት አወቃቀር ላይ ሁሉን አቀፍ ማሻሻያ እንዲደረግ በብሪክስ ጉባኤ ላይ ጠየቀች
14:25 16.05.2026 (የተሻሻለ: 14:34 16.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ተቋማት አወቃቀር ላይ ሁሉን አቀፍ ማሻሻያ እንዲደረግ በብሪክስ ጉባኤ ላይ ጠየቀች
በህንድ ኒው ዴልሂ በተካሄደው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ፤ ይበልጥ ፍትሃዊ እና ውክልናን ያማከለ ዓለም አቀፍ ሥርዓት ለመገንባት በዓለም አቀፍ አስተዳደርና ባለብዙ ወገን ተቋማት ላይ መዋቅራዊ ማሻሻያ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።
የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤትን በተመለከተ፣ ኢትዮጵያ የአፍሪካን የጋራ አቋም (በእዙልዊኒ ስምምነት እና በሲርት መግለጫ መሠረት) እንደምትደግፍ የገለጸች ሲሆን፤ የአኅጉሪቱን ውክልና የሚመለከቱ ውሳኔዎች በአፍሪካውያን እጅ ብቻ መተው እንዳለባቸው አሳስባለች።
በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ፍትሐዊ ውክልና እንዲኖርና ለአነስተኛ ገቢ ላላቸው ሀገራት ምቹ የሆነ የዕዳ ሽግሽግ ሥርዓት እንዲዘረጋ ጠይቃለች።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ፤ ከግንቦት 6 እስከ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በኒው ዴልሂ በተካሄደው የብሪክስ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ተሳትፎ ማድረጉ ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X