የአዲስ አበባን ታሪካዊና ዘመናዊ የለውጥ ጉዞ የሚዘክር አዲስ መጽሐፍ ተመረቀ
13:47 16.05.2026 (የተሻሻለ: 14:04 16.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአዲስ አበባን ታሪካዊና ዘመናዊ የለውጥ ጉዞ የሚዘክር አዲስ መጽሐፍ ተመረቀ
የመዲናይቱን ዘመናዊ ለውጥና የከተማ መልሶ ማልማት ጥረቶች በሰነድ የሚዘክረው "አዲስ አበባን እንደ አዲስ" (The Remaking of Addis Ababa: Transformation from 2020–2025) የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በይፋ ተመርቋል።
በዓለም አቀፍና በዲያስፖራ ምሁራን የተጻፈው መጽሐፉ ፣ ከከተማ ልማት በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች በሃሳብ፣ በጉልበትና በገንዘብ ያደረጉትን አስተዋጽኦ የሚዘክር እንደሆነም በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።
መጽሐፉ በእንግሊዛዊው ፕሮፌሰር ሊ፣ ክሌመንት ካቱሉሺ እንዲሁም ኢትዮጵያዊው ተወላጅ ዶክተር ሂርፖ ቁምቢ እና የምርምር ቡድናቸው የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል።
የምርቃን ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ መጽሐፉ የአዲስ አበባን ታሪካዊ ለውጥ የሚያስመዘግብ ጠቃሚ ሰነድ መሆኑን ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X