በአሜሪካ-ቻይና ውይይት፤ አሜሪካ የበላይነቱን መያዝ ያልቻለችባቸው አምስት ምክንያቶች

© telegram sputnik_ethiopiaበአሜሪካ-ቻይና ውይይት፤ አሜሪካ የበላይነቱን መያዝ ያልቻለችባቸው አምስት ምክንያቶች
በአሜሪካ-ቻይና ውይይት፤ አሜሪካ የበላይነቱን መያዝ ያልቻለችባቸው አምስት ምክንያቶች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.05.2026
ሰብስክራይብ

በአሜሪካ-ቻይና ውይይት፤ አሜሪካ የበላይነቱን መያዝ ያልቻለችባቸው አምስት ምክንያቶች

የአሜሪካ ልዑካን ቡድን ከቻይና አቻዎቻቸው ጋር በነበራቸው ድርድር የበላይነት ካለው የጥንካሬ አቋም በመነሳት መደራደር አልቻሉም ሲሉ በቻይና እና የዘመናዊ እስያ ኢንስቲትዩት የዓለም ፖለቲካ እና ስትራቴጂካዊ ትንተና ማዕከል ኃላፊ ኢካተሪና ዛክሊያዝሚንስካያ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ከዚህ ውድቀት በስተጀርባ ምን አለ?

1⃣ ከስብሰባው በፊት “አሜሪካ፣ ቻይና በነዳጅ ገቢ ምርት ላይ በእጅጉ ጥገኝነት እንዳላት በማወቅ፣ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ያላትን ቁጥጥር የማግለል (የብቸኝነት) እና የማጥበቅ እቅድ ነበራት።” ሆኖም ግን እቅዱ አልተሳካም።

2⃣ “የታይዋንን ጉዳይ እንደ ካርድ በመጠቀም የጥንካሬ የበላይነትን በሰው ሠራሽ መንገድ ለማሳየት ሙከራዎች ነበሩ።” ነገር ግን ቻይናውያን በዚህ ረገድ ሊታለፉ የማይገባቸው ቀይ መስመሮች መኖራቸውን በግልጽ አስገንዝበዋል።

3⃣ “ቻይና ይበልጥ አስቀድሞ መተንበይ የሚቻል እና ሊመራ የሚችል የሁለትዮሽ ግንኙነት ለመገንባት ትፈልጋለች።” በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመጀመሪያ የሥልጣን ዘመን በነበረው ‘የመጀመሪያው ምዕራፍ’ ስምምነት ቅር የተሰኘችው ቻይና፣ አሜሪካ ለከፈተችው የቀረጥ ጦርነት ጠንካራ ምላሽ ሰጥታለች።

4⃣ “የሩሲያ ፕሬዝዳንት ጉብኝት በቅርቡ ይጠበቅ ስለነበር፣ አሁንም ቢሆን ከጥንካሬ አቋም በመነሳት ለመደራደር የሚያስችል ምንም ዓይነት ዕድል አልነበረም።”

5⃣ “ሩሲያ በተለያዩ የጂኦፖለቲካዊ ሁኔታዎችና የውጥረት ወቅት ለቻይና እንደ ስትራቴጂካዊ አጋር እና የኋላ ደጀን ሆና ስለምታገለግል” አሜሪካ ቻይናን ጥግ ማስያዝ እና ፍላጎቷን በግድ መጫን ይከብዳታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0