የአፍሪካ ሀገራት ልማታቸውን መስዋዕት ሳያደርጉ ኢነርጂን በተመለከተ ‘ሚዛናዊ አካሄድ’ መከተል አለባቸው – የሩሲያ ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ሀገራት ልማታቸውን መስዋዕት ሳያደርጉ ኢነርጂን በተመለከተ ‘ሚዛናዊ አካሄድ’ መከተል አለባቸው – የሩሲያ ሚኒስትር

አኅጉሪቱ፣ ውድ በሆነው ርዕዮተ-ዓለማዊ የአየር ንብረት አካሄድ ከመመራት ይልቅ፣ ለገቢር ነበብ ልማቶች ቅድሚያ መስጠት እንዳለባት የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ማክሲም ሬሼትኒኮቭ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገለጹ።

“በአሁኑ ወቅት በአረንጓዴ ሽግግር ሥም ከሚተዋወቁ ቴክኖሎጂዎች መካከል አብዛኞቹ እጅግ ውድ የሆኑ ቴክኖሎጂዎች ናቸው” ሲሉ በአሩሻ ከተካሄደው የሩሲያ-ታንዛኒያ የቢዝነስ ፎረም ጎን ለጎን ተናግረዋል፡፡

እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል ሳይኖር ኢንዱስትሪዎችን፣ ከተሞችን፣ ትራንስፖርትን ወይም የአፍሪካን ህዝቦች የኑሮ ደረጃ ማሻሻል አይቻልም።

"እዚህ የድንጋይ ከሰል ክምችቶች አሉ፤ ታዲያ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለምን የአካባቢውን የድንጋይ ከሰል በማቃጠል ተመጣጣኝ የኤሌክትሪክ ኃይል አይመረትም? ለዚህም የሩሲያን ቴክኖሎጂ መጠቀም ይቻላል" ሲሉ ሬሼትኒኮቭ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0