- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

የአፍሪካ የቢዝነስ ትምህርት ለአህጉራዊ ሽግግር

የአፍሪካ የቢዝነስ ትምህርት ለአህጉራዊ ሽግግር
ሰብስክራይብ
"አብዛኞቹ የቢዝነስ ትምህርት ተቋማት ኢንዱስትሪዎችን ሳያሳትፉ የትምህርት ሥርዓቱን (ካሪኩለሙን) በራሳቸው ብቻ ያዘጋጃሉ። ዩኒቨርሲቲዎች ወይም የአካዳሚክ ተቋማት ተማሪዎቻቸውን በምድር ላይ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ሳያስተዋውቁ እንዲሁ ንድፈ-ሃሳብን ብቻ ያስተምራሉ_ ይህ ሁኔታ እንዲቀየር በትጋት ልንሰራ ይገባናል፡፡" ሲሉ የኢትዮጵያ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ የሆኑት ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታቸን የአፍሪካ የቢዝነስ ትምህርት ቤቶች የአህጉሪቱን የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን በትክክል መምራት ይችላሉ? ወይንስ አሁንም ከአካባቢያዊ እውነታዎቻችን የራቁ የውጭ ሀገራትን የትምህርት ሞዴሎች ነው እየተከተልን ያለነው? የሚሉትን ጥያቄዎች እ.ኤ.አ ከግንቦት 13 እስከ 14 ፣2026 በአዲስ አበባ በተካሄደው የAABS (African Association of Business Schools) አመታዊ ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተን ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ - የኢትዮጵያ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ፣ ፕ/ር አሊስተር ሞኮኤና — የጆሃንስበርግ ቢዝነስ ስኩል ዲን፣ ፕ/ር ኤቤኔዘር አዳኩ — የGIMPA ቢዝነስ ስኩል (ጋና)፣ ዶ/ር የቱንዴ አኒባባ — የሌጎስ ቢዝነስ ስኩል፣ ዶ/ር ሚሪያም ሙግዋቲ — የሚድላንድስ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ዲን (ዚምባብዌ) እና ዶ/ር ኢትዮጵያ ለገሰ — የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማኔጅመንት ረዳት ፕሮፌሰር አነጋግረናቸዋል፡፡

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0