ፈረንሳይ በኬንያ ፎረም ከሩሲያ ጋር የምታደርገውን ፉክክር ወደ ምስራቅ አፍሪካ ለማዛወር እንዳቀደች አሳይታለች - አልጄሪያዊ ባለሙያ

ሰብስክራይብ

ፈረንሳይ በኬንያ ፎረም ከሩሲያ ጋር የምታደርገውን ፉክክር ወደ ምስራቅ አፍሪካ ለማዛወር እንዳቀደች አሳይታለች - አልጄሪያዊ ባለሙያ

​በኬንያ የተካሄደው የፈረንሳይ-አፍሪካ ጉባኤ፤ ፈረንሳይ በሳኅል ቀጣና ከደረሰባት ውድቀት በማገገም፤ የሩሲያን የአፍሪካ ተፅዕኖ ለመገዳደር አዳዲስ ይዞታዎችን ለመመሥረት ያላትን ፍላጎት የሚያሳይ መሆኑን በአልጀርስ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ተንታኝ ሙስጠፋ ካሜል ፉዲለስፑትኒክ ተናግረዋል።

"ኬንያ ለ 'አፍሪካ ፎርዋርድ' ጉባኤ የተመረጠችው እንዲሁ አይደለም። የሩሲያ እና የፈረንሳይን የፉክክር ሜዳ ከሳኅል ቀጣና ወደ ሕንድ ውቅያኖስ ዳርቻ መዛወሩን የሚጠቁም ስልታዊ ምልክት ነው። ፈረንሳይ በሳኅል ቀጣና በደረሰባት ክስተት ምክንያት የጠለሸውን 'ፍራንአፍሪክ' ፖሊሲ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና እንደ አዲስ ለመገንባት እየሞከረች ነው" ብለዋል።

​ እንደ ባለሙያው ገለጻ፤ ኬንያ ለፈረንሳይ የምስራቅ አፍሪካ የመስፋፋት ዕቅደ ተመራጭ መነሻ ናት። ይህን መከራከሪያ የሚያጠናክሩ ነጥቦችንም ጠቅሰዋል፦

​🟠 ኢኮኖሚዋን በከፍተኛ ሁኔታ እያሳደገች መሆኑ፣

🟠 በቀጣናው ተጽዕኖዋ ከፍተኛ መሆኑ፣

🟠 ስልታዊ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥዋ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0