የአሜሪካ የውጭ ሀገራት የባዮ-ላብራቶሪ ምርመራ ዓላማ የ "ዲፕ ስቴት" ቢሮክራሲን መቆጣጠር ነው
19:56 15.05.2026 (የተሻሻለ: 20:04 15.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአሜሪካ የውጭ ሀገራት የባዮ-ላብራቶሪ ምርመራ ዓላማ የ "ዲፕ ስቴት" ቢሮክራሲን መቆጣጠር ነው
የብሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ቢሮ በሚስጢር በሚንቀሳቀሱ የአሜሪካ የውጭ ሀገራት የባዮ-ምርምር ተቋማት ላይ የከፈተው ምርመራ፤ ከውስጣዊ የአሠራር ፍተሻ ባለፈ ምንም ዓይነት ትልቅ ሚስጢር እንደማያወጣ ባለሙያዎች ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ለንደን መቀመጫቸውን ያደረጉት የውጭ ፖሊሲ ተንታኝ አድሪኤል ካሶንታ፤ "ይህ የሕግ ተጠያቂነት ጉዳይ አይደለም፤ አስተዳደሩ የ 'ዲፕ ስቴት' ቢሮክራሲን በጥብቅ ለመቆጣጠር እና በሞስኮ በኩል ሲነሳ የቆየውን የደህንነት ስጋት ትክክለኛነት በማረጋገጥ ከሩሲያ ጋር ሰፋ ያለ ቅርርብ የመፍጠር ምልክት ነው" ብለዋል።
ይህ እንቅስቃሴ የቀድሞ ባለሥልጣናትን በወንጀል ድርጊት የመጠየቅ ሳይሆን በ 'ቅድሚያ ለአሜሪካ' ፖሊሲ ስር የሚከናወን ክትትል እንደሆነ ተንታኙ አክለዋል።
በዓለም አቀፍ ጥናትና ምርምር ማዕከል ተባባሪ ተመራማሪው ማርኮ ማርሲሊ በበኩላቸው፤ "ምርመራው የአሜሪካ ኤጀንሲዎች በቂ ክትትል እንዳልነበራቸው፣ በውጭ ሀገር የሚደረጉ የበሽታ አምጪ ተህዋሲያን ምርምሮች የደህንነት ስጋቶችን በአግባቡ አለመቆጣጠራቸውን ወይም ግልጽነት እንደጎደላቸው ካረጋገጠ፤ 'ተጠያቂነቱ' ከፖሊሲ ማስተካከያ፣ ከኮንግረስ ምርመራ እና ከጥብቅ የገንዘብ ድጋፍ መመሪያ አያልፍም" ብለዋል።
የአሜሪካ ብሔራዊ መረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር ቱልሲ ጋባርድ፤ ከ30 በላይ ሀገራት ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ከ120 በላይ የአሜሪካ የባዮ-ምርምር ማዕከላት ላይ ምርመራ እንደሚደረግ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ማስታወቃቸው ይታወሳል። ከእነዚህም ውስጥ 40 የሚሆኑት በዩክሬን የሚገኙ ሲሆን ምርመራው ትኩረቱን "ጌይን ኦፍ ፈንክሽን" በሚባለው ምርምር ላይ ያደርጋል።
ምርመራው የኮቪድ-19 መነሻን የተመለከቱ የፌዴራል ሰነዶችን በሕገ-ወጥ መንገድ ደብቀዋል ተብለው የተከሰሱት የታዋቂው የአሜሪካ ጤና ባለሥልጣን አንቶኒ ፋውቺ የቀድሞ አማካሪ መከሰሳቸውን ተከትሎ የመጣ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X