አዲሱ የልማት ባንክ ኢትዮጵያን በአባልነት ለመቀላቀል እያጤነ ነው - የሩሲያ የፋይናንስ ሚኒስትር

© telegram sputnik_ethiopiaአዲሱ የልማት ባንክ ኢትዮጵያን በአባልነት ለመቀላቀል እያጤነ ነው - የሩሲያ የፋይናንስ ሚኒስትር
አዲሱ የልማት ባንክ ኢትዮጵያን በአባልነት ለመቀላቀል እያጤነ ነው - የሩሲያ የፋይናንስ ሚኒስትር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.05.2026
ሰብስክራይብ

አዲሱ የልማት ባንክ ኢትዮጵያን በአባልነት ለመቀላቀል እያጤነ ነው - የሩሲያ የፋይናንስ ሚኒስትር

"በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ፣ ኡዝቤኪስታን እና ኮሎምቢያን በአባልነት ለመቀበል እያጤንን ነው" ሲሉ​ ሚኒስትሩ አንቶን ሲሉአኖቭ ከባንኩ የሥራ አመራር ቦርድ ስብሰባ በኋላ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

የባንኩ ነባር አባላት ሀገራቱ በመቀላቀላቸው የተቋሙን ካፒታል ከማሳደግ እና የፈጠራ አጀንዳውን ከማስፋት አንጻር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል የሚል እምነት እንዳላቸውም ሚኒስትሩ ጨምረው ገልጸዋል።

 

​​ባንኩ እ.ኤ.አ በ2014 የዕድገት እና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በገንዘብ ለመደገፍ የተቋቋመ ሲሆን መሥራቾቹን ብራዚል፣ ሕንድ፣ ቻይና፣ ሩሲያ እና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በቅርብ የተቀላቀሉትን ግብፅ፣ ባንግላዲሽ፣ አልጄሪያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ያቀፈ ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0