ኢትዮጵያ በጋና በሚካሄደው 24ተኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 3ተኛውን ወርቅ አገኘች
17:45 15.05.2026 (የተሻሻለ: 17:54 15.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በጋና በሚካሄደው 24ተኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 3ተኛውን ወርቅ አገኘች
አትሌት ገመቹ ጎዳና ከፍተኛ ፉክክር በተካሄደበት የወንዶች ምድብ የ3ሺህ ሜትር መሰናክልን በድል በማጠናቀቅ ለሀገሪቱ ሦስተኛ ወርቅ አስገኝቷል።
ቀደም ሲል በተካሄዱ የ800 ሜትር እና 400 ሜትር የሴቶች የፍጻሜ ውድድሮች አትሌት ምስጋና ኃይሉ እና አጃይባ አልዩ በቅደም ተከተላቸው በአንደኝነት በማጠናቀቅ ወርቅ አምጥተዋል።
በውድድሩ የአራተኛ ቀን ውሎ ዛሬ ምሽት የ10,000 ሜትር የሴቶች ፍፃሜ የሚካሄድ ሲሆን አሰፉ አብርሃ፣ ስምረት በርሄ እና ዘይን አየልኝ ለሜዳሊያ ይፎካከራሉ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/2
© telegram sputnik_ethiopia

2/2
© telegram sputnik_ethiopia
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
2/2
© telegram sputnik_ethiopia