የዓለም ንግድ ስርዓት አፍሪካን በዓለም አቀፍ የእሴት ሰንሰለት ግርጌ ላይ ለማስቀረት የተቀረፀ ነው - ኢትዮጵያዊ ባለሙያ
17:24 15.05.2026 (የተሻሻለ: 17:34 15.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የዓለም ንግድ ስርዓት አፍሪካን በዓለም አቀፍ የእሴት ሰንሰለት ግርጌ ላይ ለማስቀረት የተቀረፀ ነው - ኢትዮጵያዊ ባለሙያ
በመሠረታዊነት በቅኝ አገዛዝ ወቅት የነበረውን የጥገኝነት ዑደት የሚያጠናክር ውስብስብ የፋይናንስ እና የንግድ መዋቅር ነው ሲሉ የፖሊሲ አማካሪ እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።
ለአፍሪካ የሚሰጥ ብድር ከሌሎች የዓለም ክፍሎች በበለጠ ከፍተኛ ወለድ ወይም ትርፍ እንዲኖረው የሚጠየቅበትን ቅድመ ሁኔታ በማሳያነት ጠቅሰዋል።
"የአፍሪካ ሀገራት ብዙውን ጊዜ የአፍሪካ የስጋት ክፍያ (ፕሪሚየም) ተብሎ የሚጠራውን አሠራር ይጋፈጣሉ። የማክሮ ኢኮኖሚ አመልካቾች የተረጋጉ ቢሆኑም እንኳ ዓለም አቀፍ የካፒታል ገበያዎች እንዲከፈቱላቸው አንዳንድ ጊዜ ከበለጸጉ ሀገራት ከሁለት እስከ ሦስት እጥፍ የወለድ መጠን ይከፍላሉ።"
የንግድ ሥርዓቱ ሌላኛው ማነቆ ሀገራቱ ለልማት እና ማኅበራዊ አገልግሎት ማዋል ያለባቸውን ገንዘብ በዕዳ ወጥመድ በመያዝ ሁሌም ብድር ከመክፈል እንዳይወጡ ማስገደዱ እንደሆነ ጠቁመዋል። በአፍሪካ የዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ዋነኛ ትኩረት ጥሬ አቃ ማውጣት ላይ መሆኑ ለአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ አለመረጋጋት መንስዔ ነው ሲሉም አክለዋል።
"በርካታ የበለጸጉ ሀገራት ጥሬ ዕቃዎች ላይ ሳይሆን በተቀነባበሩ ምርቶች ላይ ነው ከፍተኛ ቀረጥ የሚጥሉት። ይህም የአፍሪካ ሀገራት የራሳቸውን የማምረቻ ዘርፍ እንዳያዳብሩ ያደርጋቸዋል። የውጭ ኩባንያዎች የአፍሪካ ሀገራት የሚልኳቸውን ጥሬ ዕቃዎች ማቀነባበር እንዳይችሉ የሚጠቀሙበት ስትራቴጂ ነው።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X