ፕሬዚዳንት ትራምፕ ቻይና እና አሜሪካ የንግድ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ

ሰብስክራይብ

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ቻይና እና አሜሪካ የንግድ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ

በትራምፕ የቻይና ጉብኝት የተነሱ አንኳር ሃሳቦች፦

ትራምፕ ሺ ጂንፒንግን “ወዳጅ” ሲሉ በመጥራት፤ ለቻይናው መሪ ጥልቅ አክብሮት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

​ሁለቱ ሀገራት "በጣም ጥሩ የንግድ ስምምነቶች" ላይ መድረሳቸውን አመልክተዋል።

​ሺ ጂንፒንግ በበኩላቸው፤ የትራምፕ ይፋዊ የቻይና ጉብኝት ታሪካዊ እና ትርጉም ያለው እንደሆነ አንስተዋል።

​ቻይና እና አሜሪካ የተረጋጋ የንግድ ግንኙነታቸውን ለመቀጠል እና በሁሉም ዘርፎች ትብብራችውን ለማስፋፋት መግባባት ላይ መድረሳቸውን የቻይናው ፕሬዚዳንት ጠቁመዋል።

​ትራምፕ፤ ቻይና በአሜሪካ ኩባንያዎች ውስጥ በመቶ ቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ ዝግጁ ናት ብለዋል።

​የትራምፕ የቻይና ጉብኝት የጋራ መግባባትን ለማሳደግ፣ መተማመንን ለማጠናከር እና የሁለቱንም ሀገራት ሕዝቦች ደህንነት ለማሻሻል አስተዋፅኦ ይኖረዋል ሲሉ ሺ ጂንፒንግ ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0