የሱዳኑ አል-ሂላል የእግር ኳስ ክለብ የሩዋንዳ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋገጠ
14:11 15.05.2026 (የተሻሻለ: 14:14 15.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሱዳኑ አል-ሂላል የእግር ኳስ ክለብ የሩዋንዳ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋገጠ
የሱዳኑ የእግር ኳስ ክለብ አል-ሂላል የ2025/26 የሩዋንዳ ቢኬ ፕሮ-ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን የሩዋንዳ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በይፋ አስታውቋል።
አል-ሂላል፤ ጋሶጊ ዩናይትድን 2 ለ 1 በማሸነፍ ሦስት ጨዋታዎች እየቀሩት የደረጃ ሰንጠረዡን አናት በመያዝ ዋንጫውን እንደሚያነሳ አረጋግጧል።
የሱዳኑ ክለብ ሊጉን እ.ኤ.አ ከ2020 እስከ 2025 ዋንጫውን ይዞ ከቆየው የሩዋንዳው ኤ.ፒ.አር ክለብ በ14 ነጥብ በመብለጥ በ73 ነጥብ እየመራ ይገኛል።
አል-ሂላል እ.ኤ.አ በ2024–2025 የውድድር ዘመን በተመሳሳይ ወደ ሞሪታኒያ ተዛውሮ የ "ሱፐር ዲ1" ሻምፒዮንነትን በእንግድነት አሸንፏል። ይህ ተከታታይ ታሪካዊ ስኬት ክለቡ በባዕድ ሀገራት ሊጎች የበላይነቱን ያረጋገጠበት ሆኗል።
ከአፍሪካ ግንባር ቀደም ክለቦች አንዱ የሆነው አል-ሂላል፤ በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት የሀገር ውስጥ የእግር ኳስ ውድድሮች በመቋረጣቸው በውጭ ሀገራት ለመወዳደር ተገዷል። ክለቡ ከግጭት ለመሸሽ፣ የተጫዋቾቹን ብቃት ለመጠበቅ እና በአኅጉራዊ ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፈቃድ ወደ ሌሎች ሀገራት ተዛውሮ በመጫወት ላይ ይገኛል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X