ከመካከለኛው አፍሪካ የተገኘ ብርቅዬ አልማዝ በ17.3 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ
12:45 15.05.2026 (የተሻሻለ: 12:54 15.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ከመካከለኛው አፍሪካ የተገኘ ብርቅዬ አልማዝ በ17.3 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ
እ.ኤ.አ በ2000ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ የተገኘውና በዓይነቱ ልዩ የሆነው "ዘ ኦሽን ድሪም" የተሰኘው አልማዝ፤ ረቡዕ ዕለት ስዊዘርላንድ ጄኔቫ በሚገኘው የክሪስቲ የጨረታ ማዕከል ተሸጧል።
የአልማዙ ዋና ዋና ባህሪያት፦
5.50 ካራት - በዓይነቱ እስካሁን ከተገኙት ሁሉ ትልቁና ሦስት ማዕዘን ጥርብ።
በአሜሪካ የጂሞሎጂ ተቋም ዕውቅና የተሰጠው ሰማያዊ-አረንጓዴ ቀለም።
100 በመቶ ተፈጥሯዊ ቀለም - በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ዓመታት ለምድር ጨረር በመጋለጡ የተፈጠረ።
ይህ የከበረ ድንጋይ እ.ኤ.አ በ2014 ዋጋው 8.5 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ የነበረ ሲሆን በ12 ዓመታት ውስጥ ዋጋው በእጥፍ ጨምሯል። አልማዙ ለ20 ደቂቃ ያህል ከቆየ የጋለ የጨረታ ፉክክር በኋላ ስሙ ባልተጠቀሰ ገዢ መገዛቱን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X