በአላስካው የፑቲን እና ትራምፕ ውይይት ሩሲያ እና አሜሪካ ግልጽ መግባባት ላይ ደርሰዋል -የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
12:04 15.05.2026 (የተሻሻለ: 12:14 15.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በአላስካው የፑቲን እና ትራምፕ ውይይት ሩሲያ እና አሜሪካ ግልጽ መግባባት ላይ ደርሰዋል -የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ሰርጌ ላቭሮቭ በኒው ዴልሂ ከተካሄደው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ በኋላ በሰጡት መግለጫ ያነሷቸው አንኳር ነጥቦች፦
◻ የፑቲን እና ትራምፕ የግንኙነት "መንፈስ" የወዳጃነት፣ የአጋርነት እና የመከባበር ነው።
◻ በፑቲን እና ትራምፕ የአላስካ ስብሰባ በዩክሬን የሰላም ሂደት መሠረታዊ መርሆች ላይ ስምምነት ተደርሷል።
◻ ላቭሮቭ፤ ሩሲያ እና አሜሪካ በተቻለ ፍጥነት የ "አንኮሬጅ ስምምነቶችን" ያጸድቃሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
◻ ስምምነቶች ከጸደቁ በኋላ መፍትሄ የሚሹ ብዙ ጉዳዮች ይኖራሉ።
◻ ሩሲያ በቻይና እና በአሜሪካ ግንኙነት ጣልቃ አትገባም፤ ቤጂንግም ለሞስኮ እንዲህ ዓይነት "ተገቢ ያልሆኑ" ጥያቄዎችን አታቀርብም።
◻ አሜሪካ እና ቻይና የኢነርጂ ስምምነት ላይ ቢደርሱ ሩሲያ አትከፋም።
◻ ሩሲያ፤ ከአሜሪካ እና ቤጂንግ ጋር ባላት ግንኙነት "የሶስት ማዕዘን" ጨዋታ አትጫወትም፤ ይህ ሀገሪቱ የምትከተለው የዲፕሎማሲ አካሄድ አይደለም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X