የአፍሪካ ገበሬዎችን እንደ እርዳታ ተቀባዮች ማየት አቁመን ለምርምርና ፈጠራቸው እውቅና መስጠት መጀመር አለብን - የመደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት
11:43 15.05.2026 (የተሻሻለ: 11:44 15.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ገበሬዎችን እንደ እርዳታ ተቀባዮች ማየት አቁመን ለምርምርና ፈጠራቸው እውቅና መስጠት መጀመር አለብን - የመደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት
የግብርና ዕውቀት ከሰሜናዊው ዓለም የተወረሰ ነው የሚለው ትርክት ዘረኛ እና ልንጋፈጠው የሚገባ ነው የሚሉት የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ብርኸነመስቀል ጠና ናቸው።
በተቃራኒው ከምዕራባውያን የግብርና ምርምር በፊት፤ የአፍሪካ ገበሬዎች ለዘመናት ሰብሎችን የመዝራት፣ የመስኖ ስርዓቶችን የማቅናት እና የተመረጡ ዘሮችን የማዳቀል ልምድ እንደነበራቸው ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
"ልዩነቱ የምዕራባውያን ዕውቀት የተጻፈ እና ተቋማዊ መሆኑ ነው። የአፍሪካ ዕውቀት ግን በንግግር እና በልምድ ነው የሚተላለፈው። ይህ በተለየ መንገድ እንዲጠበቅ እንጂ ዋጋ እንዲያጣ አያደርገውም።"
የተቋሙ ኃላፊ ትርክቱን ለመቀልበስ መደረግ አለባቸው ያሏቸውን ሦስት ጉዳዮች ጠቅሰዋል፦
◻ ለገበሬው ተግባራዊ ሥራ ሳይንሳዊ ስያሜ መስጠት፣
◻ ለልማዳዊ ምርምርና ፈጠራ ቅድሚያ ቦታ መስጠት፣
◻ ገበሬው ምርምር እና ዕወቀቱን እንዲያዳብር ዕድል ማመቻቸት።
"የአፍሪካ ገበሬ ከውጭ መፍትሄዎችን አይጠብቅም። እሱ በየቀኑ ፈጠራ ላይ ነው። የእኛ ሥራ መሆን ያለበት ለፈጠራው እውቅና፣ ጥበቃ እና ጉልበት መስጠት ነው።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X