አፍሪካ የራሷን የወንጀል ፍርድ ቤት ለማቋቋም ምን ያህል ጊዜ ይፈጅባታል? ሱዳናዊ ባለሙያ መልስ አላቸው

ሰብስክራይብ

አፍሪካ የራሷን የወንጀል ፍርድ ቤት ለማቋቋም ምን ያህል ጊዜ ይፈጅባታል? ሱዳናዊ ባለሙያ መልስ አላቸው

ምቹ ሁኔታዎች ከተሟሉ ሙሉ በሙሉ የሚሠራ የአፍሪካ የወንጀል ፍርድ ቤት ለማቋቋም በትንሹ ከ15 እስከ 20 ዓመታት ሊፈጅ ይችላል​ ሲሉ በሩሲያ ፋይናንሻል ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ መምህር ዶክተር መሐመድ ሁሴን አብዱልዋሂድ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

​ባለሙያው በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ሀገራት በኩል እየተወሰዱ ያሉ አንዳንድ እርምጃዎችን ጠቅሰዋል፦

​◻ የሳኅል ሀገራት ጥምረት አባላት በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመመርመር የሚያስችል አማራጭ የጋራ ፍርድ ቤት ስለማቋቋም እያጤኑ ይገኛሉ።

​◻ የአፍሪካ የሰብዓዊ እና የሕዝቦች መብት ፍርድ ቤት በአሁኑ ወቅት በታንዛኒያ ሥራውን እየከወነ የሚገኝ ሲሆን የአፍሪካ ኅብረት የዚህን ፍርድ ቤት ሥልጣን በማስፋት ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ጋር እኩል የሆነ አቅም ያለው አማራጭ ተቋም ለመፍጠር አልሟል።

 

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0