- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

የአርሶ አደሮች የፈጠራ ክህሎት እና የሀገር በቀል እውቀት ሚና

የአርሶ አደሮች የፈጠራ ክህሎት እና የሀገር በቀል እውቀት ሚና
ሰብስክራይብ
“እውቀት ፓስፖርት የለውም፤ እውቀት ተግባር (ልምድ) ነው ያለው። አርሶ አደሮቻችን ምርጥ ዘር ሲመርጡ 'ዝርያ ማሻሻል'፣ ዝናብን ሲተነብዩ ደግሞ 'የጥናት ዘዴ' እንበለው፤ ለሥራቸው ሳይንሳዊ ስሙን በመስጠት የሚገባቸውን ክብር ልንሰጣቸው ይገባል፡፡ ግባችን ጥገኝነት ሳይሆን ክብር፣ ጽናትና ሀገራዊ እራስን መቻል ነው፡፡” ሲሉ የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ መሰናዶ፣ በመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት "ከአርሶ አደሮች፣ ለአርሶ አደሮች፣ በአርሶ አደሮች" በሚል መሪ ቃል የተካሄደውን ልዩ አገር አቀፍ ጉባኤ እንቃኛለን። በጉባኤው ላይ አርሶ አደሮች እንደ ተመራማሪ ቀርበው ድንች በከርሰ ምድር የማቆየት ዘዴን እና የቴምር ምርትን በአካባቢያቸው የመመረት ስኬታማ የፈጠራ ስራዎቻቸውን አጋርተዋል።
በእንግድነት የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና እና የወሃ ልማት አስተዳደር እና ሃይድሮሎጂ ረ/ፕ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ዶ/ር ዓለማየሁ አባተ ተገኝተው፣ የአርሶ አደሩን ሀገር በቀል እውቀት ከዘመናዊ ምርምር ጋር በማቀናጀት ረገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የፖሊሲ አውጪዎች ሚና ምን መሆን እንዳለበት ሰፊ ትንተና ይሰጡናል።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0