ሕንድ ለዓለም አቀፍ ግጭቶች ፍትሐዊ መፍትሄዎችን እንድምትደግፍ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

ሰብስክራይብ
ሕንድ ለዓለም አቀፍ ግጭቶች ፍትሐዊ መፍትሄዎችን እንድምትደግፍ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

​ሕንድ፤ የእስራኤል እና የፍልስጤምን ግጭት ለመፍታት የሁለት ሀገራት መፍትሄን እንደምትደግፍ በኒው ዴልሂ በተካሄደው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የመካከለኛው ምሥራቅ ቀውስ በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ እና በቀይ ባሕር ላይ የጉዞ ስጋት በመፍጠር እና የኢነርጂ መሠረተ ልማቶች እና አቅርቦቶችን በማስተጓጎል ለከፍተኛ ዓለም አቀፋዊ ቀውስ ምክንያት እንደሆነ መግለጫው አመላክቷል፡፡

ሚኒስቴሩ አስቸኳይ ትኩረት የሚሹ ሌሎች ቀውሶችንም ጠቅሷል፦

◻ በሱዳን እየደረሰ ያለው ከፍተኛ የሰው ህይወት መጥፋት፣
◻ የየመን ሰብዓዊ እና የባሕር ላይ ስጋት፣
◻ በሊቢያ የቀጠለው አለመረጋጋት።

​ በተጨማሪም ውጥረቶችን ለማርገብ እና መረጋጋትን ለመመለስ፤ ዓለም አቀፍ ሕግ እንዲከበር፣ ሲቪሎች ጥበቃ እንዲደረግላቸው እና የሲቪል መሠረተ ልማት ጥቃቶች እንዲቀሩ አሳስቧል።

የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ያደረጉት ንግግር።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0