በኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ረዳት መምህር የሙከራ ምዕራፍ ተጀመረ

© telegram sputnik_ethiopiaበኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ረዳት መምህር የሙከራ ምዕራፍ ተጀመረ
በኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ረዳት መምህር የሙከራ ምዕራፍ ተጀመረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.05.2026
ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ረዳት መምህር የሙከራ ምዕራፍ ተጀመረ

‍ ሙከራው ከ9 እስከ 12 ክፍሎችን ዒላማ አድርጎ ከኢንተርኔት ውጪ ተግባራዊ እንደሚሆንና በሂደትም በስፋት ወደ ኦንላይን ስርዓት እንደሚሰፋ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

ይህ ዘመናዊ አሠራር ኢንተርኔት ተደራሽ ባልሆነባቸው አካባቢዎች ሥርዓተ ትምህርቱን መሠረት ባደረገ መልኩ ለአስተማሪዎች ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

 

እርምጃው ከኢትዮጵያ የዲጂታል ሥነ ምህዳር ግንባታ ሂደት ጋር የሚጣጣም እና የሰው ሠራሽ አስተውህሎትን በሁሉም የመንግሥት አገልግሎት ዘርፎች ውስጥ የማዋሃድ ጥረቱን የሚደግፍ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0