ሊቢያ የሀገሪቱን ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ከ6 እስከ 12 ወራት ውስጥ ዳግም ሥራ ለማስጀመርና ምርቱን ለሀገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብ ማቀዷን አስታወቀች

© telegram sputnik_ethiopiaሊቢያ የሀገሪቱን ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ከ6 እስከ 12 ወራት ውስጥ ዳግም ሥራ ለማስጀመርና ምርቱን ለሀገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብ ማቀዷን አስታወቀች
ሊቢያ የሀገሪቱን ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ከ6 እስከ 12 ወራት ውስጥ ዳግም ሥራ ለማስጀመርና ምርቱን ለሀገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብ ማቀዷን አስታወቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.05.2026
ሰብስክራይብ

ሊቢያ የሀገሪቱን ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ከ6 እስከ 12 ወራት ውስጥ ዳግም ሥራ ለማስጀመርና ምርቱን ለሀገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብ ማቀዷን አስታወቀች

እ.ኤ.አ ከ2013 ጀምሮ ሥራ አቁሞ የቆየው የራስ ላኑፍ የነዳጅ ማጣሪያ በቀን 220 ሺህ በርሜል የማምረት አቅም ይኖረዋል ሲሉ የብሔራዊ ነዳጅ ኮርፖሬሽን ሊቀመንበር መሥዑድ ሱሌይማን ገልጸዋል።

​ የብሔራዊ ነዳጅ ኮርፖሬሽን (ኖክ) ሰኞ ዕለት እንዳስታወቀው፤ ትራስታ የተባለው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አጋር ከሌርኮ የጋራ ኩባንያ መውጣቱን ተከትሎ፣ ለዐሥር ዓመታት የዘለቀው የግልግል ዳኝነት ክርክር በማብቃቱ የማጣሪያ ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ሆኗል።

"ይህ ስምምነት በሊቢያ የነዳጅ እና ጋዝ ዘርፍ ውስጥ ካሉ እጅግ ውስብስብ ጉዳዮች አንዱን በቋሚነት የሚዘጋ ሲሆን ከሀገሪቱ ዋና ዋና የነዳጅ እና የፔትሮኬሚካል ሀብቶች አንዱን ሙሉ በሙሉ ወደ ሊቢያውያን ቁጥጥር ይመልሳል። በተጨማሪም ለማገገሚያ፣ ለሥራ ማስጀመሪያ እና ለልማት አዲስ ምዕራፍና መንገድ ይከፍታል" ሲል መግለጫው አስነብቧል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0