"የሱዳን ሰላም እጦት ለኢትዮጵያም የሰላም እጦት ነው" - ኢትዮጵያዊ ምሁር
09:40 14.05.2026 (የተሻሻለ: 09:44 14.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
"የሱዳን ሰላም እጦት ለኢትዮጵያም የሰላም እጦት ነው" - ኢትዮጵያዊ ምሁር
ሚያዚያ 7፣ 2015 ዓ.ም የተጀመረው የሱዳን ጦርነት ሀገሪቱን ለተለያዩ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ፍላጎት ያላቸው ኃይሎች የሽኩቻ ሜዳ እንዳደረጋት በዲላ ዩኒቨርስቲ መምህር እና የፖለቲካ ተመራማሪ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የግጭቱ መዘዝ የኢትዮጵያን በር እያንኳኳ ከመሆኑ አኳያ፤ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፤ ቀላል ባይሆንም ሰላም ለማምጣት የበኩሏን ሚና መጫወት እንዳለባት ጠቁመዋል።
"ኢትዮጵያ የተዋናዮቹን ፍላጎት በተወሰነ ደረጃ በማስማማት በሱዳን ዘላቂ ሰላም ማምጣት ትችላለች፤ ምክንያቱም የሱዳን ሰላም እጦት ለኢትዮጵያም የሰላም እጦት ነው።"
የሱዳን ሰላም ለክልሉ፣ ለአኅጉሪቱ እና በአጠቃላይ የሰው ልጅ ስላም እንደሆነ ሊሠመርበት የሚገባ ጉዳይ ነው ሲሉም ባለሙያው አጽንኦት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X