በአዲስ አበባ የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ቁጥር ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ መምጣቱ ተነገረ
19:09 13.05.2026 (የተሻሻለ: 19:14 13.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በአዲስ አበባ የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ቁጥር ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ መምጣቱ ተነገረ
የሀገሪቱ መዲና ባለፉት ዘጠኝ ወራት 9.5 ሚሊዮን ጎብኚዎችን እንደሳበች የከተማዋ የቱሪዝም ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ይህ ቁጥር ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ጭማሪ የታየበት እንደሆነ የኮሚሽኑ ኃላፊ ሁንዴ ከበደ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል፡፡
እንደ ኮሚሽኑ ገለጻ የጎብኚዎቹ ስብጥር፦
▪1.1 ሚሊዮን የውጭ ሀገራት፣
▪8.4 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ የሀገር ውስጥ ጎብኝዎች ነበር፡፡
በኮሪደር ፕሮጀክቶች እና በመሠረተ ልማት ዝርጋታዎች ያበበችው አዲስ አበባ፤ ከቅርብ ግዜያት ወዲህ የስፖርት ዝግጅቶች፣ የተለያዩ ጉባኤዎች፣ ፌስቲቫሎች እና ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች ማስተናገዷ የውጭ ቱሪስቶችን በስፋት እንድትስብ አስችሏታል ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X