የመካከለኛ ምሥራቅ ቀውስ የገበያ መደራሻችንን ማስፋት እንዳለብን አስተምሮናል - የኢትዮጵያ የሥጋ አምራቾችና ላኪዎች ማኅበር
17:11 13.05.2026 (የተሻሻለ: 17:14 13.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የመካከለኛ ምሥራቅ ቀውስ የገበያ መደራሻችንን ማስፋት እንዳለብን አስተምሮናል - የኢትዮጵያ የሥጋ አምራቾችና ላኪዎች ማኅበር
ከሀገሪቱ የሥጋ ምርት መዳረሻ 90 በመቶውን የሚሸፍነው የመካከለኛው ምሥራቅ በቅርቡ በአሜሪካ እና ኢራን ጦርነት መታመሱን ተከትሎ በተፈጠረው የበረራ መስተጓጎል ለአጭር ግዜም ቢሆን የዘርፉ የወጪ ንግድ እንቅስቃሴ ተጠቅቶ እንደነበር የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ካሊድ ካሊፋ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል፡፡
ሆኖም ከረመዳን ጾም ጋር ተያይዞ በሳዑዲ አረቢያ የነበረውን ከፍተኛ ፍላጎት በመጠቀም የዩኤኢ ትዕዛዞችን ማዞር በመቻሉ ችግሩ እንደታለፈ አብራርተዋል፡፡
“አማራጭ የገበያ መዳረሻ መፈለግ እንዳለብን ከባድ ትምህርት ሰጥቶናል። አሁን በትጋት እየሠራንበት ነው። ወደ አፍሪካ ሀገራት ለመላክ በጅማሮ ላይ ነን። በእስያ ደግሞ የኢትዮጵያን የበሰለ ስጋ ለመላክ ከቻይና መንግሥት ጋር ስምምነት ለመፈራረም የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰናል።”
ከአፍሪካ ከሶማሊያ፣ ጊኒ፣ አልጄሪያ፣ ቱኒዚያ እና ሞርኮ ጋር ከወዲሁ የንግድ ግንኙነት መፈጠሩን ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X