ከተኩስ አቁም ድርድሩ በፊት ዩክሬን ከዶንባስ መውጣት አለባት - ክሬምሊን
16:01 13.05.2026 (የተሻሻለ: 16:04 13.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ከተኩስ አቁም ድርድሩ በፊት ዩክሬን ከዶንባስ መውጣት አለባት - ክሬምሊን
ኪየቭ መሻቷ የተኩስ አቁም እና ሙሉ የሰላም ድርድር ከሆነ ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የዩክሬን ኃይሎች ከዶንባስ እና ሌሎች የሩሲያ ግዛቶች እንዲወጡ ማዘዝ አለበት ሲሉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ገልጸዋል።
ቃለ አቀባዩ በመግለጫቸው ያነሷቸው ሌሎች ዋና ዋና ነጥቦች፦
የተኩስ አቁም የሚደረገው የዩክሬን ኃይሎች ከሩሲያ ክልሎች ሲወጡ ብቻ ነው።
ወደፊት የሚካሄዱ የዩክሬን ድርድሮች እጅግ አስቸጋሪ እና በርካታ ሚስጢራዊ ዝርዝሮችን ያካተቱ ይሆናሉ።
ሩሲያ ዩክሬንን አስመልክቶ ከአሜሪካ ጋር መደበኛ ግንኙነት እያደረገች ነው።
ሞስኮ፤ ዋሽንግተን ጉዳዮችን ከዩክሬን ጋር ማያያዟን ስታቆም ሰፊ የሩሲያ-አሜሪካ የትብብር ፕሮጀክቶች ወደ ትግበራ ይሸጋገራሉ የሚል ተስፋ አላት።
ቭላድሚር ፑቲን በቅርቡ የተደረገውን የሳርማት ባሊስቲክ ሚሳይል ሙከራ አድንቀዋል።
የሳርማት ሙከራዎች ለሩሲያ የረጅም ጊዜ ደህንነት ወሳኝ ናቸው።
ሩሲያ እንደ ሳርማት ያሉ ሚሳኤሎችን ስታስወነጭፍ በዓለም አቀፍ አሠራር መሰረት ሌሎች ሀገራት አስቀድመው እንዲያወቁ ታደርጋለች።
ሞስኮ ስለ ሳርማት ሙከራ እስካሁን ከአሜሪካ ይፋዊ ምላሽ አልደረሳትም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X