ጅቡቲ የ160 ሚሊዮን ዶላር ሁለገብ የነዳጅ ማከማቻ ማዕከል ግንባታ ጀመረች
19:56 12.05.2026 (የተሻሻለ: 20:04 12.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ጅቡቲ የ160 ሚሊዮን ዶላር ሁለገብ የነዳጅ ማከማቻ ማዕከል ግንባታ ጀመረች
በስልታዊው የዳመርጆግ ኮሪደር ውስጥ የሚገነባው ይህ የነዳጅ ማከማቻ፤ የአፍሪካ ሀገራት በአቅርቦት ሰንሰለት መቆራረጥ እና ተለዋዋጭ የነዳጅ ገበያዎች እየተፈተኑ ባሉበት ወቅት የመጣ በመሆኑ እንደ ትልቅ ምዕራፍ ተቆጥሯል።
ይህን ግዙፍ ማከማቻ በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙት ወደቦች፣ መንገዶች እና ቀጣናዊ የንግድ ኮሪደሮች ጋር በማስተሳሰር ለኢትዮጵያ እና ለሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ቁልፍ መዳረሻ ለማድረግ ታልሟል።
ማከማቻው በቀጣናው እየጨመረ የመጣውን የነዳጅ ምርቶች ፍላጎት ለመሙላት የሚገነባ የተቀናጀ የሎጂስቲክ እና ንግድ ማዕከል ይሆናልም ተብሏል።
በ22 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፈው ተርሚናል፤ 400 ሺህ ሜትሪክ ቶን በሚገመት የማከማቸት አቅም ጅቡቲን በአፍሪካ ቀንድ እና በምስራቅ አፍሪካ ቁልፍ የኢነርጂ ማከፋፈያ መናኃሪያ ያደርጋታል ሲሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X