ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ኡጋንዳ ዘርፈ ብዙ ትብብራቸውን ለማጠናከር ስድስት ስምምነቶችን ተፈራረሙ

ሰብስክራይብ

ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ኡጋንዳ ዘርፈ ብዙ ትብብራቸውን ለማጠናከር ስድስት ስምምነቶችን ተፈራረሙ

የኮንጎ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው፤ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ እና የኮንጎ አቻቸው ፌሊክስ ሺሴኬዲ ግንቦት 4 ቀን በካምፓላ ተገናኝተው "ወዳጃዊ እና ውጤታማ ውይይት" አድርገዋል።

የተፈረሙት ስምምነቶች የሚከተሉትን ዘርፎች ያካትታሉ፦

◻ ንግድ፣

የወጪ ንግድ ምርቶች እና ነፃ የንግድ ቀጣናዎች፣

ቱሪዝም፣

ቴሌኮም እና ኢንተርኔት፣

የመንግሥት አስተዳደር፣

ፍለጋ እና የነፍስ አድን።

በተጨማሪም ሁለቱ ወገኖች በሃይድሮካርቦን (ነዳጅ እና ጋዝ)፣ በኢነርጂ እና ድንበር ተሻጋሪ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮጀክቶች ዙሪያ መወያየታቸው ተገልጿል።

የተፈረሙት የመግባቢያ ሰነዶች በፍጥነት ወደ ትግበራ እንደሚገቡ ተረጋግጧል።

ፕሬዳንት ሙሴቬኒ ጉብኝቱ "የሁለቱን ሀገራት የጋራ ዕጣ ፈንታ ይበልጥ የሚያጠናክር ነው" ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0