የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የተፈጸመው “ታሪካዊ በደል” እንዲታረም ጥሪ አቀረቡ

© telegram sputnik_ethiopiaየአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የተፈጸመው “ታሪካዊ በደል” እንዲታረም ጥሪ አቀረቡ
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የተፈጸመው “ታሪካዊ በደል” እንዲታረም ጥሪ አቀረቡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.05.2026
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የተፈጸመው “ታሪካዊ በደል” እንዲታረም ጥሪ አቀረቡ

​ሊቀመንበሩ ማህሙድ አሊ ዩሱፍ፤ አፍሪካ በምክር ቤቱ ቋሚ ውክልና እንዲኖራት ጥያቄ  የምታቀርበው ታሪካዊ በደልን ለማረም እንጂ ልዩ ጥቅም በመሻት እንዳልሆነ በናይሮቢው የአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባኤ ላይ ተናግረዋል።

“የጸጥታው ምክር ቤት ተዓማኒነት እና ሕጋዊነት የሚወሰነው በ1945ቱ የጂኦፖሊቲካ አሰላለፍ ሳይሆን የዛሬውን ዓለም እውነታዎች በማንፀባረቅ አቅሙ ላይ ነው” ሲሉ አክለዋል።

አፍሪካ ድምጽን በድምጽ መሻርን ጨምሮ ቢያንስ ሁለት ባለ ሙሉ መብት ቋሚ መቀመጫዎች እንዲሁም በሚስፋፋው ምክር ቤት ውስጥ አምስት ቋሚ ያልሆኑ መቀመጫዎችን መጠየቋን እንደምተቀጥል በድጋሚ አስረግጠዋል ሲል የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን መግለጫ ተነቧል።

 

የአኅጉሪቱ የሥነ-ህዝብ፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተፅዕኖ እያደገ ነው ያሉት ዩሱፍ፤ “ከዚህ በኋላ ከቋሚ ውክልና ተገልላ መቆየት አትችልም” ብለዋል።

 

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0