በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ያለውን የትምህርት ትስስር የሚያጠናክር የመግባቢያ ስምምነት በጅግጅጋ እና በሱዳኑ ሲናር ዩኒቨርሲቲ መካከል ተፈረመ
15:59 12.05.2026 (የተሻሻለ: 16:04 12.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ያለውን የትምህርት ትስስር የሚያጠናክር የመግባቢያ ስምምነት በጅግጅጋ እና በሱዳኑ ሲናር ዩኒቨርሲቲ መካከል ተፈረመ
ስምምነቱ የሁለቱን የትምህርት ተቋማት ትብብር እንደሚያጠናክር እና በጋራ የተጠቃሚነት መስኮች የእውቀት እና ሙያ ልውውጥን እደሚያበረታታ ጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ አስታውቋል፡፡
የሱዳኑ የትምህርት ተቋም ልዑካን በጅግጅጋ በነበራቸው ቆይታ ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በስልታዊ የትብብር መስኮች ማለትም፦
በጋራ የምርምር ሥራዎች፣
በድህረ-ምረቃ ሥልጠናዎች፣
በልውውጥ ፕሮግራሞች፣
በፈጠራ ቴክኖሎጂዎች እና የምርጥ ተሞክሮዎች ሽግግር ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
በተጨማሪም የመግባቢያ ስምምነቱ ውጫዊ ኃይሎች በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት መካከል ውጥረት እንዲነግስ ከሚያደርጉት ጥረት በተቃራኒ፤ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተግባራዊ እርምጃዎችን እየወሰዱ እንደሚገኙ የታየበት ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/2
© telegram sputnik_ethiopia

2/2
© telegram sputnik_ethiopia
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
2/2
© telegram sputnik_ethiopia