በደቡብ አፍሪካ በተከሰተው ዓውሎ ነፋስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 10 ደረሰ
15:24 12.05.2026 (የተሻሻለ: 15:34 12.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በደቡብ አፍሪካ በተከሰተው ዓውሎ ነፋስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 10 ደረሰ
በጎርፍና ነፋሱ የሚደርሰው ከፍተኛ ጉዳት መቀጠሉን ተከትሎ፤ መንግሥት በስድስት ግዛቶች ውስጥ የተፈጥሮ አደጋ ግዜ አዋጅ አውጇል፡፡ ዌስተርን ኬፕ በከፍተኛው ከተመቱ ግዛቶች ዋነኛው መሆኑን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ዓውሎ ነፋሱ ያስከተላቸው ዋና ዋና ጥፋቶች፡-
🟠 በቤቶች እና መሠረተ ልማቶች ላይ የደረሰው ሰፊ ውድመት፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲፈናቀሉ እና የኤሌክትሪክ ኃይላቸው እንዲቋረጥ አድርጓል፣
🟠 በርካታ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ እና መንገዶች፣ የተራራ ማለፊያዎች እና የበረራ ሥራዎችን ጨምሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ መስተጓጎል እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፣
🟠 በጎርፍ መጥለቅለቅ፣ በወንዞች መፍሰስ እና በግድቦች መደርመስ ስጋት ምክንያት ብዛት ያላቸው ነዋሪዎች አካባቢያቸውን እንዲለቁ ትዕዛዝ ተላልፏል።
ሁለተኛውና ይበልጥ ኃይለኛው ቀዝቃዛ አየር ከምዕራብ አቅጣጫ ወደ ደቡብ አፍሪካ እየተቃረበ መሆኑን የሜትሮዎሎጂ ተመራማሪዎች አስጠንቅቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia
© telegram sputnik_ethiopia
© telegram sputnik_ethiopia