አይኤምኤፍ ኢትዮጵያ የኢነርጂ ድጎማዎችን ወይም መጠነ ሰፊ የታክስ ቅነሳዎችን እንዳታደርግ መከረ
14:54 12.05.2026 (የተሻሻለ: 15:21 12.05.2026)

ሰብስክራይብ
አይኤምኤፍ ኢትዮጵያ የኢነርጂ ድጎማዎችን ወይም መጠነ ሰፊ የታክስ ቅነሳዎችን እንዳታደርግ መከረ
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂየቫ፤ ከመካከለኛው ምሥራቅ ቀውስ ጋር ተያይዞ የነዳጅ እጥረት፣ የዋጋ መናር እና የአቅርቦት መስተጓጎል የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እየፈተኑ እንደሆነ ለመንግሥት ሚዲያ በሰጡት ቃል ገልጸዋል፡፡
የገንዘብ አበዳሪው ኃላፊ፤ አንዳንድ የዋጋ ጭማሬዎች አይቀሬ እንደሆኑ በቃለ መጠይቃቸው የገለጹ ሲሆን ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት እና ተጋላጭ ማኅበረሰቦችና አባወራዎችን ለመደገፍ ሀብትን በአግባቡ መጠቀም የተቋማቸው ምክር እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡
“አሁን በከፍተኛ ዋጋ ምክንያት የመጣውን ቀውስ የሚያርዝሙ፤ የኃይል ድጎማ ወይም ሰፊ የግብር ቅነሳን ለመሰሉ ላልታለሙ እርምጃዎች ጊዜው አይደለም።”
ሆኖም ሀገሪቱ ግጭቱ በጀመረበት ወቅት በጥሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አቋም ላይ ከመገኘቷ አኳያ፤ ቀውሱ በአጭሩ ከተቋጨ በዕድገት፣ በክፍያ ሚዛን እና በዋጋ ግሽበት ላይ የሚኖረው ጫና መጠነኛ እንደሚሆን ክሪስታሊና ጆርጂየቫ ጠቁመዋል፡፡
“ኢትዮጵያ በባለሥልጣናት በተካሄደው ማሻሻያ አማካኝነት፤ ወደ ንዝረቱ እየገባች ያለችው (በቀውሱ የተፈጠረው) ከጥንካሬ አቋም በመነሳት ነው።”
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X