በኬንያ እየተካሄደ የሚገኘውን የፈረንሳይ ጉባኤ በመቃወም ሰልፎች ተካሄዱ

ሰብስክራይብ

በኬንያ እየተካሄደ የሚገኘውን የፈረንሳይ ጉባኤ በመቃወም ሰልፎች ተካሄዱ

​ሰልፎቹ በኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እና በፈረንሳዩ ኢማኑኤል ማክሮን በሚመራው የ "አፍሪካ ፎርዋርድ" ጉባኤ ማጠቃለያ፤ ፓን-አፍሪካኒዝም ሰሚት አጌንስት ኢምፔሪያሊዝም በተሰኘው ድርጅት የተዘጋጁ ናቸው።

​ በኬንያታ አቬኑ ሰልፈኞች ላይ የአስለቃሽ ጭስ እንደተተኮሰባቸውና በርካቶችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ገልጿል።

​አክቲቪስቶች በ"ኡፉንጋማኖ ሃውስ" ለተቃውሞ ጉባኤ በመሰባሰብ፤ "ዳግም ቅኝ አገዛዝን" እና በምስራቅ አፍሪካ የፈረንሳይ ወታደራዊ መስፋፋትን ለመቃወም ወደ ኬንያ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል አቅራቢያ ለመንቀሳቀስ እየሞከሩ ነው።

​ የሀገሪቱ ብሔራዊ የፖሊስ አገልግሎት በማዕከላዊ የንግድ ዲስትሪክት ከፍተኛ የደህንነት ኃይል በማሰማራት፤ የጉባኤውን ሥፍራ እና የዓለም አቀፍ ተወካዮችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲቲ ሆል ዌይ እና ሀራምቤ አቬኑን ጨምሮ ዋና ዋና መንገዶችን ዘግቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0