ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ልምምድ ላይ በገጠማት ድንገተኛ ህመም ሕይወቷ አለፈ

አትሌት የብርጓል መለሰ
አትሌት የብርጓል መለሰ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.05.2026
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ልምምድ ላይ በገጠማት ድንገተኛ ህመም ሕይወቷ አለፈ

ባለትዳርና የሁለት ልጆች እናቷ አትሌት የብርጓል መለሰ፤ ዛሬ ማለዳ ልምምዷን እየሠራች ባለችበት ወቅት ህመም ተሰምቷት ለህክምና በሄደችበት ሆስፒታል በሞት እንደተለየች የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

የ36 ዓመቷ የብርጓል የፓሪስ ግማሽ ማራቶንን ሁለት ጊዜ፣ ሊዝበን ግማሽ ማራቶንን አንድ ጊዜ እንዲሁም የሻንጋይ፣ ፕራግና ሂውስተን ማራቶንን በበላይነት አጠናቃለች፡፡

በ2015ቱ የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በግማሽ ማራቶን ለኢትዮጵያ የነሀስ ሜዳሊያ አስገኝታለች፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0