የዚምባብዌ በወርቅ የተደገፈ ኢኮኖሚ 'አስተማማኝ ውጤቶችን' እያመጣ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ገለፁ

ሰብስክራይብ

የዚምባብዌ በወርቅ የተደገፈ ኢኮኖሚ 'አስተማማኝ ውጤቶችን' እያመጣ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ገለፁ

ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የሀገሪቱን የወርቅ እና የዚግ (የዚምባብዌ መገበያያ ገንዘብ) መጠባበቂያ ክምችት ለማረጋገጥ የዚምባብዌ ማዕከላዊ ባንክ ካዝናዎችን በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል።

"ከ4 ሜትሪክ ቶን በላይ የወርቅ እና የውጭ ምንዛሪ ክምችት ስላለን፣ የዚግ ገንዘባችን ሙሉ በሙሉ የተደገፈ እና ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ድንጋጤዎችን የመቋቋም አቅም ያለው ነው" ብለዋል።

እነዚህ ክምችቶች ዝም ብለው ቁጥሮች ብቻ ሳይሆኑ የሀገሪቱን የገንዘብ ሉዓላዊነት የሚደግፉ እውነተኛ ሀብቶች መሆናቸውን ፕሬዝዳንቱ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

"እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ 5 ሜትሪክ ቶን የማድረስ ግባችን ላይ ለመድረስ እየሠራን ባለበት በዚህ ወቅት፣ ለሁሉም ዚምባብዌውያን የተረጋጋ፣ ግልጽ እና የበለጸገ ኢኮኖሚ ለመገንባት ያለንን ቁርጠኝነት እናረጋግጣለን።" ብለዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0