ናይጄሪያ በትምህርት ቤቶች አዲስ የዕፅ ምርመራ መመሪያ ይፋ ማድረጓ ተዘገበ
17:08 11.05.2026 (የተሻሻለ: 17:14 11.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ናይጄሪያ በትምህርት ቤቶች አዲስ የዕፅ ምርመራ መመሪያ ይፋ ማድረጓ ተዘገበ
በትምህርት ቤቶች ደህንነቱ የተጠበቀ የመማሪያ ከባቢን ለመፍጠር እና የተማሪዎችን የትምህርት አፈፃጸም ለመጠበቅ ሲባል፤ አስገዳጅ የዕፅ ምርመራን የሚያስፈጽም "ብሔራዊ የትግበራ መመሪያ" በሥራ ላይ እንደሚውል የአገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
እንደ መገናኛ ብዙሃኑ ዘገባ ከሆነ እርምጃዎቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
በተደጋጋሚ ጥፋተኛ ለሚሆኑ ተማሪዎች የምክር አገልግሎት፣ ሕክምና እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከትምህርት ገበታ መታገድ፣
ለሁሉም አዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች አስገዳጅ የዕፅ ምርመራ ማድረግ፣
በትምህርት ዘመኑ በሙሉ በዘፈቀደ እና በመደበኛነት የሚደረግ ድንገተኛ የዕፅ ምርመራና
ማንኛውንም ሕገ-ወጥ ዕፅ መያዝ ወይም መጠቀም ላይ የተጣለ ጥብቅ እገዳ።
አዲሱ መመሪያ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ተማሪዎች በሦስት ደረጃ በሚከናወን የምርመራ ሂደት ለመለየት ያለመ መሆኑ ተገልጿል። በምርመራው ውጤታቸው አዎንታዊ ሆኖ የተገኘ ተማሪዎች በትምህርት ቤቱ ባለስልጣናት በሚወሰን የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና ውስጥ እንዲያልፉ ይደረጋል።
የማኅበራዊ ሚዲያ ቪዲዮ፦ በናይጄሪያ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X