ኢትዮጵያ የቱሪዝም ሀብቶቿን በዶሃ የቱሪዝም ማስተዋወቂያ መድረክ ላይ አቀረበች

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የቱሪዝም ሀብቶቿን በዶሃ የቱሪዝም ማስተዋወቂያ መድረክ ላይ አቀረበች

በኳታር ዶሃ “ኢትዮጵያን ይጎብኙ፡ የሰው ዘር መገኛንና የተፈጥሮ ድንቆችን ይመርምሩ” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው 4ኛው የኢትዮጵያ ቱሪዝም ማስተዋወቂያ ፎረም፤ ሀገሪቱ ያላትን እምቅ የቱሪዝም እና የኢንቨስትመንት ዕድሎች አስተዋውቃለች።


በኳታር የኢትዮጵያ አምባሳደር ፈይሰል አሊይ በፎረሙ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ፣ የቡና መፍለቂያ እና የራሷ ፊደልና ቀመር ያላት የጥንታዊ ሥልጣኔ ባለቤት መሆኗን ገልጸዋል።


አምባሳደሩ አክለውም እንደ አዲስ የተገነቡትን የአንድነትና ወዳጅነት ፓርኮች፣ ወንጪ፣ ጎርጎራ እና በለሳ የመሳሰሉ ግዙፍ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለተሳታፊዎች አስተዋውቀዋል።

መድረኩ በኢትዮጵያና በኳታር መካከል ያለውን የቱሪዝም ትብብር ለማጠናከር ያለመ እንደነበር ተገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0