የሩሲያ "አፍሪካ ኮርፕስ" የነዳጅ ኮንቮይ ወደ ባማኮ ሲጓዝ በማጀብ የጋራ ጥበቃ አከናወነ

ሰብስክራይብ

የሩሲያ "አፍሪካ ኮርፕስ" የነዳጅ ኮንቮይ ወደ ባማኮ ሲጓዝ በማጀብ የጋራ ጥበቃ አከናወነ

🟠 የአፍሪካ ኮርፕስ እንደገለጸው፣ እሁድ ዕለት ከሩሲያ ክፍለ ጦር የተላኩ ሄሊኮፕተሮች ወደ ማሊ መዲና የሚጓጓዘውን የነዳጅ አቅርቦት ደህንነት አስከብረዋል።

🟠 ቀደም ብሎም ግንቦት 1 ቀን፣ በአፍሪካ ኮርፕስ እና በማሊ ጦር የተዋቀረ የጋራ የጥበቃ ቡድን በደቡብ ምዕራብ ማሊ በካቲ እና ኪታ ከተሞች መካከል ጥበቃ ማድረጉን አክሎ ገልጿል።

የጥበቃ ስራው በስኬት መጠናቀቁንና "የማሊ ዜጎች ወታደሮቹን በማየታቸው መደሰታቸውን" ክፍለ ጦሩ ገልጿል።

እ.ኤ.አ. በ 2023 በሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር ስር የተመሰረተው አፍሪካ ኮርፕስ፤ በአፍሪካ ደህንነትን የመጠበቅ፣ ሽብርተኝነትን የመዋጋት እና የአካባቢውን ኃይሎች የማሰልጠን ኃላፊነት ተጥሎበታል።

ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም የሩሲያ ክፍለ ጦር በህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድኖች ተዘጋጅቷል የተባለውን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የማሊ ጦር እንዲያከሽፍ ረድቷል።

  ቪዲዮው፣ አፍሪካ ኮርፕስ ሄሊኮፕተር የነዳጅ ቦቴ መኪኖችን ሲያጅብ ያሳያል፡፡   

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0