ኢትዮጵያዊው ገጣሚ በዕወቀቱ ሥዩም በባርሴሎና ዓለም አቀፍ የግጥም ፌስቲቫል ላይ ሥራዎቹን ሊያቀርብ ነው
13:29 11.05.2026 (የተሻሻለ: 13:41 11.05.2026)

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያዊው ገጣሚ በዕወቀቱ ሥዩም በባርሴሎና ዓለም አቀፍ የግጥም ፌስቲቫል ላይ ሥራዎቹን ሊያቀርብ ነው
በሥነ-ጽሑፍ ሥራዎቹ ተወዳጅነትን ያተረፈው ደራሲ እና ገጣሚ በዕወቀቱ ሥዩም ከግንቦት 6 እስከ 13 ቀን 2018 ዓ.ም በስፔን ባርሴሎና በሚካሄደው 41ኛው ዓለም አቀፍ የግጥም ፌስቲቫል ላይ በክብር እንግድነት እንዲሳተፍ መመረጡ ተዘግቧል።
በዕወቀቱ ግንቦት 13 በ‘ፓላው ዴ ላ ሙዚካ ካታላና’ አዳራሽ በሚካሄደው የፌስቲቫሉ መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ከመጡ ሰባት ዝነኛ ገጣሚዎች ጋር በመሆን የግጥም ሥራዎቹን ያቀርባል።
የኢትዮጵያን ታሪክ ከመረመረበት "ከአሜን ባሻገር" መጽሐፉ ባሻገር፣ "ኗሪ አልባ ጎጆዎች"፣ "በራሪ ቅጠሎች"፣ "የ'ሣት ዳር ሐሳቦች" እና "የማለዳ ድባብ" በሚሉ የግጥም መድብሎቹ የሚታወቀው በዕወቀቱ፤ የሀገረሰባዊ የግጥም ለዛን ከዘመናዊ የፈገግታና የቁም ነገር ስልት ጋር በማዋሃድ የዘመኑ የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ተጠቃሽ ባለሙያ ተደርጎ ይወሰዳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X