ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ ስምንት ወራት ብቻ ከሥጋ ወጪ ንግድ 87 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቷ ተዘገበ

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ ስምንት ወራት ብቻ ከሥጋ ወጪ ንግድ 87 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቷ ተዘገበ

የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በዋነኛነት ሳዑዲ ዓረቢያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ የሥጋ ምርት መዳረሻ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሥጋ አምራችና ላኪዎች ማኅበር አስታውቋል፡፡

የአፍሪካ አኅጉር አቀፍ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ተከትሎ ወደ ጋና እና ሶማሊያ ምርት እየተላከ መሆኑን የገለፁት የመኅበሩ ፕሬዝዳንት ከሊፋ ሁሴን፣ የሥጋ ተረፈ ምርት ደሞ ወደ ቬትናም እና ሆንግ ኮንግ እንደሚላክ ጠቁመዋል።

በዘርፉ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን ተከትሎ ወደ ውጭ የሚላክ የስጋ ምርት በመጠንና በገቢ በከፍተኛ መጠን ማደጉንም ፕሬዝዳንቱ ለሀገር ውስጥ ሚድያ ገልፀዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0