በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት ሽፋን 86.3 በመቶ ደርሷል – ጤና ሚኒስቴር
11:24 11.05.2026 (የተሻሻለ: 11:48 11.05.2026)

ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት ሽፋን 86.3 በመቶ ደርሷል – ጤና ሚኒስቴር
ሚኒስቴሩ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠው የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት ሽፋን 64 በመቶ ከነበረበት ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።
የማኅበረሰቡን የጤና ተሳትፎ ለማሳደግ የሚረዱ የጤና በጎ ፈቃደኞች አጠቃቀም ቀደም ሲል በ4 ወረዳዎች ብቻ ተወስኖ የነበረው ሲሆን፣ አሁን ላይ ወደ 330 ወረዳዎች እንዲያድግ ተደርጓል።
በመጀመሪያ ደረጃ የጤና ተቋማት አገልግሎት የተመላላሽ ታካሚዎች ቁጥር በ2013 ዓ.ም የነበረው 111 ሚሊዮን፣ በ2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት ብቻ ወደ 233.8 ሚሊዮን ከፍ ማለቱንም ሪፖርቱ ያሳያል።
ይህም ማለት በአሁኑ ወቅት 80 በመቶ የሚሆኑ ታካሚዎች ሕክምናቸውን የሚያገኙት በቅርባቸው በሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ ክፍሎች መሆኑን ሪፖርቱ ያመለክታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X